በረቂቅ ሕግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ የቀረበ ጥሪ
የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒት ቁጥጥር መመሪያ በአዋጅ 1112/2011 መረሰት የተከለሰና አዲስ የናርኮቲክ እና ሳይኮትሮፒክ መድኃኒት ቁጥጥር ረቂቅ መመሪያ የተዘጋጀ በመሆኑ በረቂቁ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የረቂቁን ቅጂ ከባለስልጣኑ ድረ-ገጽ www.edfa.gov.et ላይ በማውረድ ወይም ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ማተሚያ አካባቢ በሚገኘው የባለስልጣኑ ዋና መስሪያ ቤት ህግ ክፍል በአካል በመቅረብ በመውሰድ እስከ የሚያዚያ 10 ቀን 2016 ከቀኑ 9፡00 ድረስ በጽሑፍ ለባለስልጣኑ የሕግ ክፍል ቢሮ ቁጥር 204 ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ contactefda@efda.gov.et ወይም በፖስታ ቁ. 5681 እንድትልኩ በአክብሮት ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በነጻ ስልክ መስመር 8482 በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡”
የኢትዮጵያ የምግብ እና መደኃኒት ባለስልጣን፡፡