ከጨርቅ የተሠራ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ከኮሮና ቫይረስ ራሴን ለመጠበቅ ይረዳኛል?

የኮረና ቫይረስ በሽታ አምጪ ተሕዋስያን በዓይን የማይታዩ በጣም ረቂቅ ስለሆኑ በቤት ውስጥ ከጨርቅ የሚዘጋጁ የፊት ጭንብሎች በበሽታው ከተያዘ ሰው የሚወጡ በቫይረሱ የተበከሉ የእርጥበት ቅንጣቶችን መከላከል እንደማያስችሉ የተለያዩ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ፡፡ በሌላ  በኩል ደግሞ ሀገራት እነዚህን ከጨርቅ የተሠሩ የፊት ጭንብሎች በማህበረሰቡ ቢደረጉ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ስለሚረዳ ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን ከመጠበቅ ጎን ለጎን ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ጭንብል ቢጠቀሙ…

ከጨርቅ የተሠራ የፊት መሸፈኛ ጭንብል በማምረት ለገበያ ማቅረብ ብፈልግ ምን ማድረግ አለብኝ?

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከጨርቅ የተሠራ የፊት መሸፈኛ ጭንብል ለማምረት አምራቾችና አከፋፋዮች ሊከተሏቸው የሚገቧቸውን አሠራሮች በተመለከተ ያወጣውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እና የገበያ ፈቃድ አሰጣጥ መመሪያ ይህንን http://www.fmhaca.gov.et/covid19-publications/ መጫን ማግኘት ይችላሉ፡፡