በረቂቅ ህግ ላይ አስተያየት እንዲሰጥ
የኢትዮጰያ የምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ 1112/2011 አንቀፅ 72(1) በተሰጠው ስልጣን መሰረት አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 531/2013 የተከለሰ በመሆኑ በረቂቁ ላይ አስተያየት ለመስጠት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ከባለስልጣኑ ድረ-ገጽ የተፃነውን ረቂቅ መመሪያ በማውረድ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ሸዋ ዳቦ ፊትለፊት ፀሀይ ባንክ ያለበት ህንፃ ላይ የባለስልጣኑ መስሪያ ቤት የህግ አገልግሎት የስራ ክፍል በሮ 11ኛ ህንፃ ቁጥር 105 በአካል በመቅረብ ወይም በኢ-ሜይል አድራሻ contactefda@efda.gov.et ወይም በፖስታ ቁ. 5681 እስከ ግንቦት 15 ቀን 2017 ከቀኑ 11፡00 ድረስ በጽሑፍ እንድትልኩ በአክብሮት ጥሪ ያስተላልፋል፡፡
የኢትዮጵያ የምግብ እና መደኃኒት ባለስልጣን!